ነሲሀ ኢስላማዊ የዉይይት መድረክ Ethio Nesiha Group

ነሲሀ ኢስላማዊ የዉይይት መድረክ
Ethio Nesiha Group
www.nesiha.com
===========
"من يرد الله به خيرا يفقهه في الدين" رواه البخاري ومسلم
"አላህ መልካም የሻለትን (ሰው) ዲኑን ያስገነዝበዋል" (ቡኻሪና ሙስሊም)
• “ነሲሀ ኢስላማዊ የዉይይት መድረክ” መሰረታዊ የዲን እዉቀትን ለመለዋወጥ አላማ ብቻ በዲን ተማሪዎች የተመሰረተ ግሩፕ ነው። በተለያዩ የዲን አጀንዳዎች ዙርያ በሸሪዓዊ ስርዓትና አዳብ ፤ ሀሳብ ለመለዋወጥ፣ ለመወያየት፣ ለመጠያየቅ እና ለመማማር ለሚፈልጉ ሁሉ ክፍት መድረክ ነው። ስለዚህም፤ ወቅታዊ ጉዳዮች፣ ጠቅላላ እውቀት፣ ስፖርት፣ ጤናና መሰል ርእሶች አይስተናገዱበትም።
• ይህ ግሩፕ የኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተርን ወይም ሌሎች ኢስላማዊ ተቋማትን የሚወክል አይደለም። ለማንኛዉም ተሳታዊ ክፍት በመሆኑ ጽሁፎች የሚወክሉት የጸሀፊያቸዉን አቋም እና አመለካከት ብቻ ነው።
• የዳእዋ ስራ አማና በመሆኑ ግሩፑን በመጠቀም ማዕከላዊዉን የአህሉሱና አቋም የሚጻረሩ ተሳትፎዎችን በማስተላለፍ የአባላትን አመለካከት መበረዝ ለማንም አይፈቀድም። ስለሆነም፤ እንዲህ አይነት ተሳትፎዎች ሁሉ ቦታ አያገኙም።
• ማካፈል የምትፈልጉትን መልዕክት አጭር እና ግልጽ በሆነ ቋንቋ “በአማርኛ” ፓስት ለማድረግ ሞክሩ። አማርኛን ለመጻፍ ከተቸገራችሁ ይህንን ሊንክ ተጠቀሙ http://www.google.com/transliterate/Amharic
• እውቀትን መሰረት ያደረገ ተሳትፎ ብቻ የሚስተናገድበት እንጂ ሁሉም ሰው ያማረንውን ጽሁፍ ሁሉ ለአባላት የሚያካፍልበት ግሩፕ አይደለም። አባል የሆነ ሁሉ የግድ ተሳትፎ አይጠበቅበትም፤ ስለሆነም ኢስላማዊ እውቀትን ለማካፈል ብቃት ካለው ሰው ማስተማር፤ ተማሪ ከሆነ ሰው ደግሞ ከሚያስተምሩ ወንድሞችና እህቶች መማር የሚጠበቅ ነው።
• ጠቃሚ የሆኑ እና ጊዜ ወስዳችሁ ያዘጋጃችኋቸው ጽሁፎች እንዳይባክኑ ዶክሜንት ውስጥ ፖስት ብታደርጓቸው ለአባላት ከደረሱና ከተነበቡ በኋላ በማንኛዉም ጊዜ በቀላሉ ልንደርስባቸው እንችላለን።
• በየጊዜው አዳዲስ ጓደኞችን ወደ ግሩፑ በማስገባት የበኩልዎን አስተዋጽኦ ያበርክቱ። ለመልካም ነገር ሰዉን ማመላከት የማይቋረጥ ምንዳን ያስገኛልና እስካሁን ጓደኞቻችሁን ያላስገባችሁ ካላችሁ አሁኑኑ ጊዜ ስጡት።
• ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶችን ስናርምም ሆነ ስንተች ጥሩ ቃላትን በመጠቀም አርአያ እንሁን።
• ቪዲዮ ወይም ፒክቸር ፖስት ስታደርጉ አጠር ያለ ማብራርያ ብታክሉበት መልካም ነው። መረጃ የሚሆኑ ነገሮችን ካልሆነ በቀር በጽሁፍ መተላለፍ የሚችሉ ተራ መልዕክቶችን በቪዲዮ ፖስት ባይደረጉ ይመረጣል።

Ethio Nesiha Group is dedicated for sharing Pure knowledge In-shaa'llah.. We focus on basic Islamic Lessons Aqidah, Fiqh,
Hadith...etc
- you can share evidence based articles for Lessons & refutations.
- do not post links for sites, or long articles, quote the statements you want to share so that members read your massage easily .
'Uthmaan (radhi-yallaahu 'anhu) said:((Knowledge is better than wealth; Knowledge protects you and you (have to) protect wealth)). Al-Khateeb in "Al-Faqeeh wal-Mutafaqqih" - Volume 1,
=================
Important notice: The views expressed in the posts do not necessarily represent the views of Ibnu Mas'oud Islamic center.


የግሩፑ አስተባባሪ
አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ
አላህ መልካሙን ሁሉ ይግጠመን