Yedil Qen የድል ቀን

ጥቂት ስለ እኛ፡


እኛ ከተለያዩ ብሄረሰቦች የተውጣጣን የተለያዩ ቋንቋዎች የምንናገር የተለያየ ሀይማኖት ያለን ለዘመናት የተነሱብን አምባገነን አገዛዞች ነጻነት አሳጥተውን ከሰው በታች አድርገው ያዋረዱን መሆናችን አንድ ያደረገን ለነጻነታችን፣ ለሰውነት ክብራችን የቆምን ኢትዮጵያውያን ነን።እኛ ኦሮሞነታችን፣አማራነታችን፣ ሶማሌነታችን፤ ዳውሮነታችን፤ትግሬነታችን፣ ወዘተ ሳያግደን በኢትዮጵያዊነታችን አብረን ሌሎች በአገራቸው የተጎናጸፉትን ነጻነት እኛም በተራችን ልንጎናጸፍ የተነሳን ኩሩ ኢትዮጵያውያን ነን። እኛ ነጻነት የተራብን፣ኑሮ ያማረረን፣ ዘረኝነት ያንገፈገፈን፣ ዴሞክራሲ የተጠማን ኢትዮጵያውያን በግብጽና በቱኒዚያ የተደረገውን አይነት አብዮት በአገራችን ልናስነሳ፣ ልንመራውና በአገራችን ዴሞከራሲ ልናሰፍን ከነፍሳችን ተማምለን ተነስተናል። የተመኘነውን እውን እስክናደርግ ምንም ዓይነት ምድራዊ ሃይል አያቆመንም። እስካሁን በአገራችን በተነሱት አገዛዞች ማለትም በአጼው ፊውዳላዊ፣ በደርጉ ወታደራዊ፣ በወያኔ ዘረኛ፤ አፋኝና አረመኔ አገዛዝ የተማረርን ነጻነታችንን የምንወድ በሌሎች ነጻነት እየቀናን መኖር የማንሻ ኩሩ ኢትዮጵያውያን ነን።

በአገራችን ከዚህ ቀደም ተነስተው ከነበሩ አብዮቶች ትምህርት የቀሰምን ኢትዮጵያውያን ነን። ለነጻነት የተደረጉ አብዮቶችን ምሳሌ ፍለጋ ሩቅ መሄድ እንደማያስፈልገን ተረድተናል። ከዚህ ቀደም በአገራችን ተማሪዎችና የፊውዳሉ ስርአት ዘረፋ ያንገፈገፋቸው ጭሰኞች አብዮት አስነስተው የአጼውን ፊውዳላዊ አገዛዝ እንደጠራረጉት እናውቃለን። ከዚያም በሗላ በ1997 ሚያዚያ 30 ላይ ከሁለት ሚሊዮን ህዝብ በላይ አደባባይ ሲወጣ ተመልክተናል። ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ የለም እኮ የሚለን ካለ ከዚህ ቀደም በአገራችን እንደታየው ዛሬም በቱኒዚያና በግብጽ እንደተደገመው የነጻነት አብዮት ለማስነሳት የፖለቲካ ድርጅቶች አያስፈልጉም ነው መልሳችን። አንድ ትልቅ ትምህርት ቀስመናል አገዛዞች ሁሉ እድሜያቸው የሚወሰነው በእኛ የፍርሃት ልክ እንደሆነ። ስለዚህም ላንፈራ ቃል ገብተናል።

የወያኔን ገዳይነት የሚነግሩን ሁሉ ፈርተን እንድንቀመጥ ሊያደርጉን እንደሆነ አውቀን ከኛ ዘንድ ቦታ የላችሁም ሂዱልን እንላቸዋለን። ወያኔ እኮ ገዳይ ነው ለሚሉን ቤን አሊም ሙባረክም እኮ ገዳዮች ነበሩ ነው መልሳችን። ታሪክ የሚነግረን የቱንም ያህል ጠንካራ የሆነ ምድራዊ አምባገነን ለነጻነቱ ቆርጦ በተነሳ እና በተባበረ የህዝብ ሃይል ፊት እንደ ጉም ሲበን ነው። ውድ ኢትዮጵያውያን ነጻነታችንን የምንጎናጸፍበት ቀን ተቃርቧል። መጻኢ እድላችን የሚወሰነው እያንዳንዳችን ዛሬ በምንወስደው አዎንታዊ እርምጃ ነው። አምላክ ከኛ ጋር ነው።


Who we are:

We are a group of Ethiopians with varying religious and ethnic backgrounds who have organized ourselves for a noble purpose that will determine how we live the rest of our lives and the life we inherit to the next generation of Ethiopia.

Understanding that, although we have always been proud to have maintained our independence from foreign colonizers, as long as we have lived, we have always been the personal properties of successive tyrants who have dehumanized and humiliated us below subhuman standards.

Recognizing that our diverse cultural beauty has been used as an instrument for few ethnocentric tyrants to divide and rule us with iron fist, we have joined hand to hand to re-affirm to them that we are a people of one nation – that we are proud Ethiopians!

Knowing that it has always been the motto of benevolent tyrants to preach Armageddon in a post-dictatorship era, we express our firm belief that our lives cannot get any worse than today's humiliating ethnic apartheid in Ethiopia.

Inspired by the Tunisian and Egyptian people who have ascertained the ownership of their God-given rights as citizens of their respective nations as well as the ongoing battle of the Libyan people for freedom, we are determined to use the prevailing spirit of liberty that has engulfed the north of our continent to remove the illegal regime imposed upon Ethiopia by force.

Mindful of the scare tactics used to terrorize us into submission, we are rising up in unison to prove once again that no brute power can defeat a proud and united nation and that the TPLF regime will blow into dust when faced with the wrath of an oppressed people.

We appeal to the international community to stand with us and humbly express that, more than any of the essentials of life, we Ethiopians crave for justice, freedom and democracy - the ability to determine our future, the future of our children, and the fate of our beloved nation.

We still do have confidence in the victory of GOOD over EVIL!
God Almighty is on our side!