ዜና ቤተክርስቲያን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ (Ethio. Orthodox Tewahido Church News)

የአባቶቼን ርስት እሰጥህ ዘንድ እግዚአብሔር ያርቅል፡፡ነገስት ፳፡፫ (1ነገ.20፡3)
"" መሰረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ እንዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል።የእህዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የተከበረ ነገር ይባላል። የሚያውቁኝን ረዓብንና ባቢሎንን አስባቸዋለሁ እንሆ ፍልስጤማውያን ጢሮስም የኢትዮጵያም ሕዝብ እነዚህ በዚያ ተወለዱ። ሰው እናታችን ጽዮን ይላል በውስጥዋም ሰው ተወለደ እርሱ ራሱም ልዑል መሰረታት። እግዚአብሔር ለህዝቡ በውስጥዋም ለተወለዱት አለቆችዋ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል። በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል። መዝ 86(87) : 1 - 7 ።
ሕግ ከጽዮን ይወጣል የተባለው የኦሪት መጨመሪያ በሚሆን በወርቅ በተለበጠው ታቦት ውስጥ የሚጠብቀው የመሐላ ጽላት ሕግ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም የተባለ ንጹሕ የእግዚአብሔር ቃል ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱ ነው ፡፡ ከኢየሩሳሌም ሰዎች ወገን የዕብራውያን ልጅ ናትና እንደ ተጻፈ እንዲህ ሲል፤
የኢየሩሳሌም ልጅ ደስ ይበልሽ የጽዮንም ልጅ ኃሤት አድርጊ ፡፡ የጽዮን ልጅ በማለቱ የሐዋርያትን ቤተሰብ ቤተክርስቲያንን ይጠራታል የእስራኤልን አምላክ ማደሪያ ጽዮንን እናት አድርጎ የሐዲሱ ሕግ ከብሉይ ተገኝቷልና፡፡ (ዘካ ፱÷፱ ) +++
"እለት እለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሃሳብ ነው።" ፪ቆሮ.፲፩፡፳፰